ድሬዳዋ ካፈራቻቸው ትላልቅ ጥበበኞች መካከል አንዱ የሆነውና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ዘፈኖቹ በስፋት የሚታወቀው ተወዳጁ አርቲስት መሀዲ አብዱረህማን ወይም በቅፅል ስሙ ‘መሀዲ ጢቃ” ትላንትና ምሽት ባደረበት ድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ ሲሆን፤ የድሬዳዋ አስተዳደርም በአርቲስቱ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል።
አርቲስት መሀዲ ትላንት ምሽት በተሰማው ድንገተኛ ህመም ለህክምና እርዳታ ሆስፒታል ተወስዶ አስፈላጊው ድጋፍ ቢደረግለትም ህይወቱን ማትረፍ ሳይቻል ቀርቷል።
አርቲስቱ በተለይም “በሬዱ ባዲያ” (Bareedduu Baadiyyaa) ተብሎ በሚጠራው ተወዳጅ አልበሙ እውቅናና ዝናን ያተረፈ ሲሆን በርካታ የጥበብ ስራዎችንም ለአድማጮችና ለአድናቂዎቹ አድርሷል። አርቲስቱ በስራው ታታሪና ለሙያውም ከፍተኛ ፍቅር ያለው የነበረ ሲሆን የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበር።
በድጋሚ የድሬዳዋ አስተዳደር በአርቲስቱ ህልፈት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለመላው ቤተሰቦቹ፣ለወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ እንዲሁም ለመላው የጥበብ አፍቃሪያን መፅናናትን ይመኛል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር !!


