የቻይና ኢንቨስተሮች በድሬደዋ የተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ተገለፀ::

በኢትዮጵያ የቻይና ኢምባሲ ምክትል አምባሳደር ሚስተር ሱን የተመራ ልዑክ በድሬደዋ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ጉብኝት ያደረገ ሲሆን ከአስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይቷል።

በውይይቱ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፉ አቶ ገበየው ጥላሁን ድሬዳዋ ከአራት የቻይና ከተሞች ጋር የህትማማች ግንኙነት እንዳላት ገልፀው በአስተዳደሩ የቻይና ባለሀብቶች በፌደራል መንግስቱ በኩል በበርካታ የኢንቨስትመንትና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ ፍላጎት እንደለ ተናግረዋል።

ድሬዳዋ በተለይም በሶስት ዋናዋና ዘርፎች ማለትም ግብርና በማኑፋክቸሪንግና ኢንቨስትመንትን እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፍ በአጠቃላይ አስራ ሰባት በጥናት የተለዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች መኖራቸውን ገልፀው የቻይና ባለሀብቶች በነዚህ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና ኢምባሲ ምክትል አምባሳደር ሚስተር ሱን በበኩላቸው የቻይና ለአለም አቀፉ ኢኮኖሚ 30 በመቶ ድርሻ እንዳላት ፣ እንዲሁም የፈጠራና የምርምር መፍለቂያ መዐከል መሆን መቻሏን ገልፀዋል።

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በባቡር መስመር ፣በማእድን ፣በኢንዱስትሪ ፣ ማኑፋክቸሪን ዘርፎች ያለውን የጠበቀ ትብብር ይበልጥ ማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ምክትል አምባሳደሩ ተናግረዋል።የውጪ ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ሰላም ፣አሰሪ የሆነ ፖሊሲ እንዲሁም መሰረተ ልማት ወሳኝ መሆኑን ያስታወሱት ምክትል አምባሳደሩ ድሬደዋ እነዚህ ሁኔታዎች በአንፃራዊነት የተሻለ መሆኑን ጠቁመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *