የውሀ አምራች ፋብሪካዎች ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረጋቸው አስተዳደራዊ እርምጃ ተወሰደ::

በአስተዳደሩ የውሀ አምራች ፋብሪካዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በራሳቸው ተነሳሽነት ባደረጉት የዋጋ ጭማሪ ተጠቃሚውን ማህበረሰብ ይቅርታ ጠይቀዋል።

ከአስተዳደሩ ንግድ እንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ጋር ውይይት ያደረጉት የውሀ አምራች ፋብሪካ ባለቤቶች እና ስራ አስኪያጆች እንደተናገሩት አለማቀፋዊ የገበያ ሁኔታ ተከትሎ የጥሬ እቃው መጨመር ጋር ተያይዞ ከሁለት ወራት በላይ ዋጋ ቢጨምርም ዋጋ ሳይጨምሩ መቆየታቸውን እና አሁናዊ የጥሬ እቃ ዋጋ ጭማሬ ግን ዋጋ እንዲጨምሩ ምክንያት እንደሆናቸው ገልፀዋል።

የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ በ6:00ሰዓት ውስጥ የአስተዳደሩ ንግድና ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ቢሮ በነበረ ዋጋ እንዲሸጥ በታዘዝነው መሰረት ቀደም ባለው ዋጋ መልሰው እየሸጡ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በቀጣይ ህብረተሰቡን ያማከለ የዋጋ ጭማሪውን ለማድረግ ለአስተዳደሩ ጥያቄ ማቅረባቸውን ጠቁመዋል።

የአስተዳደሩ ንግድና ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኡሱማን አህመድ በሰጡት አቅጣጫም ነዋሪው ማህበረሰብ ተፈጥሮአዊ ውሀ ጨውነት ስላለው የታሸገና የተጣራ ውሀ ይጠቀማሉ ይህም በመሆኑ ያለአግባብ ዋጋ በመጨመር ማህበረሰቡ ላይ ጫና መፍጠር አስተዳደራዊ እርምጃ ያስወስዳል ብለዋል።

አስተዳደሩ ለኢንደስትሪዎች ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የገለፁት ም/ኃላፊው ኢንደስትሪዎች የማምረት አቅማቸው እንዲጨምርና ውጤታማ እንዲሆኑ በዘርፉ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን በተጠናከረ መልኩ የመፍታት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ይህም በመሆኑ በውይይት የተነሱ የጥሬ እቃ የዋጋ ጭማሪ አስተዳደሩ ያለበትን ደረጃ አጥንቶና አጣርቶ እስኪያጣራ ባለበት ዋጋ እንዲሸጡ እና ጭማሪው ታይቶ ሲጨምር ከጅምላ ሻጭ እስከ ችርቻሮ ያለው ጭማሪ ህብረተሰቡን ያማከለ እንዲሆን ይደረጋል ብለዋል።

ዋጋ ጭማሪ ማድረግ ካስፈለገ አስፈላጊነቱ በጥናት ተረጋግጦና

ማህበረሰቡን ያማከለ ተደርጎ ፍትሀዊ በሆነ መልኩ በህግ አግባብ ይፋ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ አመላክተዋል።

በቦቴ ውሀ ወደ ፋብሪካቸው በማስገባት ለተለያየ ፍጆታ የሚያውሉ የውሀ አምራች ፋብሪካዎች በቦቴ ውሀ ወደ ፋብሪካቸው ማስገባት ፈፅሞ የተከለከለ ነው ሲሉም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የአስተዳደሩ ንግድና ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ቢሮ ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሚኑ ጠሀ በውይይቱ የተነሱ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ምላሽ እንደሚሰጡ በመጠቆም ያልተገቡ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ የንግዱ ማህበረሰብ ለመቆጣጠር የክትትልና ቁጥጥር ስራ እስከ ወረዳ ድረስ ያሉ አመራሮች በራሳቸው ውሳኔዎችን እንዲወስኑና እርምጃ እንዲወስዱ የኃላፊነት ስልጣን እንደተሰጣቸው ገልፀዋል።

አቶ አሚኑ አክለውም በመካከለኛው ምሥራቅ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ የተፈጠረውን ቀውስ በማስመልከት ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ማነስ የዋጋ ጭማሪውን እንዳባባሰው ገልፀው ችግር ለመቅረፍ አቅርቦት እንዲጨምርና ገበያ ላይ በስፋት የምርት አቅርቦቱ እንዲጨምር ተቋማቸው እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል ።

ይህን ተግባራዊ ሳያደርጉ የተገኙ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃም አስተዳደሩ ሊወስድ እንደሚገደድ ኃላፊው አቶ አሚኑ ጠሀ ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *