የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች እዝ 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በታላቅ ወታደራዊ ትዕይንት እያከበረ ነው።
ኢትዮጵያ በትውልድ ቅብብሎሽ ሀገር ያጸኑ የበርካታ ጀግኖች ምድር ናት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች እዝም ባለፉት 65 ዓመታት በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ የማይበገር ጽናት ይዞ ኢትዮጵያን ያኮራ ጀብዱ ፈጽሟል ብለዋል።
እዙ አሁን ላይ በመከላከያ ሪፎርም ስራዎች አማካኝነት አየር ወለድ፣ ኮማንዶ እና ልዩ የጸረ ሽብር ኃይል በመያዝ በአደረጃጀት፣በሠው ኃይል እና በትጥቅ ዘመኑን በዋጀ መልኩ ተዋቅሮ በየትኛውም ጊዜና በማንኛውም ሁኔታ ግዳጁን በብቃት ለመፈጸም በአስተማማኝ ቁመና ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።
እዙ 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ሲያከብር የገነባውን የዘመነ ወታደራዊ አቅም፣ የሰው ኃይል ዝግጁነት እና የታክቲክ ብቃት ለሕዝብ ይፋ አድርጓል።
በተለይም ዛሬ የቀረበው የተቀናጀ የውሃ ላይ ልምምድ ፣ የአየር ወለድና የኮማንዶ አባላት በቅንጅት ያሳዩት ልዩ ልዩ ወታደራዊ ክህሎት የሠራዊቱን ከፍተኛ ብቃት ያረጋገጠ ነው ብለዋል።


