ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቄለም ወለጋ ዞን ሃዋ ገላን ወረዳ ተገኝተው በ”ሌማት ትሩፋት” መርሃ-ግብር የለማ የሙዝ እርሻን በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል።
አርሶ አደሮቹ መሬትና የውኃ ኃብትን በአግባቡ በመጠቀም፣ ባህላዊ የመስኖ ዘዴዎችን በማቀናጀት አካባቢያቸውን ወደ ተስፋ ሰጪ የግብርና ማዕከልነት መለወጣቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ተመልክተዋል።
በተለይም የመንገድ መሠረተ ልማት መገንባት የአርሶ አደሩን ምርት በቀላሉ ወደ ገበያ ለማድረስ የፈጠረው ዕድል እጅግ የሚያበረታታ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የልማት ጥረቶች ከማኅበረሰቡ ፍላጎት ጋር ሲናበቡ የሚገኘውን ውጤት በተግባር መመልከታቸውን ገልጸዋል።


