የቄጦ የመስኖ ፕሮጀክት፤ ለሰዲ ጫንቃ እና ሃዋ ገላን ወረዳዎች አዲስ የልማት ተስፋ::

ለሰዲ ጫንቃ እና ሃዋ ገላን ወረዳዎች ትርጉም ያለው ለውጥ እያመጣ የሚገኘው የቄጦ የመስኖ መሠረተ ልማት ፕሮጀክት ለግብርናው ዘርፍ አዲስ ገጽታ እየፈጠረ ይገኛል።

ፕሮጀክቱ የአካባቢውን የተፈጥሮ መልክዓ-ምድር በአግባቡ በመጠቀም፣ ለግብርና ሥራ የማይቋረጥ የውኃ አቅርቦት እንዲኖር ታስቦ የተተገበረ ነው።

በአሁኑ ወቅትም የመስኖ ሥራውን በቀጥታ ጥቅም ላይ በማዋል የታረሰ እና የለማ መሬት ለኅብረተሰቡ ጉልህ ፋይዳ ማስገኘት ጀምሯል።

ከመስኖው ጋር አብሮ የተገነባው የመንገድ መሠረተ ልማትም የገበያ ተደራሽነትን በማስፋት የነዋሪዎችን የቀን ተቀን የኑሮ እንቅስቃሴ በእጅጉ አቅልሏል።

አካባቢው ሰፊ የግብርና እምቅ አቅም ያለው እንደመሆኑ እንደ ስንዴ፣ ሩዝ፣ ሙዝ፣ ፓፓያ እና ብርቱካን ያሉ ምርቶች በስፋት እንዲመረቱ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል።

ይህ ስራ የመስኖ እና የመሠረተ ልማት ቅንጅት ለዘላቂ የገጠር ግብርና ልማት እድገት ምን ያህል ወሳኝ መሆኑን በተግባር ያሳየ ትልቅ አብነት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *