እነዚህ ስምምነቶች በኢትዮጵያ እና በቱርክዬ መካከል እየተጠናከረ የመጣውን አጋርነት ይበልጥ የሚያጎለብቱ ሲሆን፤ ሁለቱ ሀገራት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በተመሰረቱ መስኮች፤ ያላቸውን የሥራ ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውን አመላካች ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት ረጀብ ጣይፕ ኤርዶዋን በ9ኛው የቱርክ-ኢትዮጵያ የጋራ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ስምምነት ሰነድ እንዲሁም በኢነርጂ ዘርፍ በትብብር ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።


