የድሬደዋ አስተዳር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር
የቀቤና ልማት ማህበር እና ልዩ ወረዳ ያዘጋጁት የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ የተኳሄደ ሲሆን በአስተዳደሩ የሚኖሩ የቀቤና ተወላጆች በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ለሚገኝው ልዩ ዞን የሚያደረጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጠሉ ጥሪ ቀርቧል።
የድጋፍ መረሀ ግብሩ በልዩ ወረዳው ለሚገነባው አዳሪ ትምህርት ቤት እና ጠቅላላ ሆስፒታል የገቢ ማሰባሰቢያ ነው።
በኹነቱ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በልማት ውጤታማ ከሆኑ ወረዳዎች ውስጥ አንዱ መሆኑን ገልፀው የድሬደዋ አስተዳደር ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ይሱፍ በበኩላቸው የብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ጥያቄዎችን ከመለሰባቸው አካባቢዎች መካከል የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አንዱ ማሳያ መሆኑን ገልፀው በድሬዳዋ ከተማ የሚኖሩ የቀቤና ብሄር ተወላጆች ለወረዳው ልማት ያሳዩትን ድጋፍ በመጪው ምርጫም ሊደግሙት ይገባል ሲሉ አስታውቀዋል ።
የቀቤና ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ አሚን በተፈጥሮ እና ባህላዊ ሀብቱ የሚታወቀው አካባቢው የልማት ጥያቄ ለመመለስ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራሙ መዘጋጀቱን ገለፀው በተለይም ጠቅላላ ሆስፒታል እና አዳሪ ትምህርት ቤት ለመገንባት የሚያሰፈልገውን አንድ ቢሊዮን ብር በማሳካት በወረዳው የሚታየውን የትምህርት ቤት እና የጤና ተቋማት እጥረት ይቀረፋል ሲሉ ገልፀዋል ።
በዝግጅቱ ላይ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ እና የካቤኔ አባላት እንዲሁም የቀቤና ልዩ ወረዳ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችን ጨምሮ የብሄረሰብ ተወላጆች ተገኝተዋል።


