ኢትዮጵያ 39ኛውን የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ በስኬት አስተናግዳለች – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር::

ኢትዮጵያ 39ኛውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት ማስተናገዷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ብሔራዊ የዝግጅት ኮሚቴ ሰብሳቢና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በሰጡት መግለጫ፤ ጉባኤው የኢትዮጵያን የላቀ የመስተንግዶ አቅም፣ አስተማማኝ የጸጥታ ሁኔታና ጨዋነት የተሞላበት የእንግዳ ተቀባይነት ባህል በተግባር ያስመሰከረ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ስኬት ሊመዘገብ የቻለው በሕዝባችን ትዕግሥትና እንግዳ ተቀባይነት፣ በጸጥታና…

Read More

39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔና የጣሊያን አፍሪካ ጉባዔ በስኬት መጠናቀቃቸውን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ

በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤና 2ኛው የጣሊያን አፍሪካ ጉባዔ በስኬት መጠናቀቃቸውን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል፡፡ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይሉ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ፤ የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ደኅንነት የበለጠ በማጠናከር በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ እጀባና አስተማማኝ ጥበቃ በማድረግ ጉባኤዎቹ በሰላም እንዲጠናቀቁ ማስቻሉን ገልጿል። መላው የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አመራርና አባላት የተሰጣቸውን…

Read More

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ልማትን ለመደገፍ በወገንተኝነት እንቆማለን።

የድሬደዋ አስተዳር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር የቀቤና ልማት ማህበር እና ልዩ ወረዳ ያዘጋጁት የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ የተኳሄደ ሲሆን በአስተዳደሩ የሚኖሩ የቀቤና ተወላጆች በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ለሚገኝው ልዩ ዞን የሚያደረጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጠሉ ጥሪ ቀርቧል። የድጋፍ መረሀ ግብሩ በልዩ ወረዳው ለሚገነባው አዳሪ ትምህርት ቤት እና ጠቅላላ ሆስፒታል የገቢ ማሰባሰቢያ ነው። በኹነቱ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ::

አዲሱን የኅብረታችን ሊቀመንበር፤ የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬን አግኝቼ በተረከቡት ኃላፊነት ደስታዬን ገልጬላቸዋለሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። የአፍሪካውያን ጠንካራ ትብብር እና ቀጣናዊ ግንኙነቶችን ለማሳደግ በሚያስችሉ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተወያዩ::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሁለተኛው ቀኑን ከያዘው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን፣ ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም፣ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ጋር ተወያዩ::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ጋር ተወያይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ “ዛሬ ከኬንያ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ጋር በአኅጉራዊ የቅድሚያ ጉዳዮች እና የወል ፍላጎቶቻችን ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል” ብለዋል።

Read More

“ሴቶችን በየዘርፉ ማሳተፍ ሀገርን እንደ ማሳተፍ ይቆጠራል” – ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው::

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በ30ኛው የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች የልማት ተቋም (OAFLAD) ጉባኤ ላይ በመገኘት ንግግር አድርገዋል። ቀዳማዊት እመቤቷ በንግግራቸው፤ የዘንድሮው የ30ኛው የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች የልማት ተቋም ጉባኤ “የአፍሪካን ሴቶች ፈተናዎችን የመቋቋም ዐቅም መገንባት፡- የአየር ንብረት፣ ግጭቶች እና ዘላቂ ነገ” በሚል መሪ ሃሳብ መካሄዱን ገልጸዋል። ይህ መሪ ቃልም በጾታ እኩልነት፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ ዘርፍ እና በአየር…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከናሚቢያ ፕሬዚዳንት ኔቱምቦ ናንዲ ንዴትዋ ጋር ተወያዩ::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከናሚቢያ ፕሬዚዳንት ኔቱምቦ ናንዲ ንዴትዋ ጋር ተወያይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ከናሚቢያ ፕሬዝዳንት ኔቱምቦ ናንዲ ንዴትዋ ጋር በአኅጉራዊ ጉዳዮች እና የትብብር ዘርፎች ላይ ሃሳብ መለዋወጣቸውን ገልጸዋል።

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጋና ፕሬዚዳንት ጆን ማሃማ ጋር ተወያዩ::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሁለተኛው ቀን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን ከጋና ፕሬዚዳንት ጆን ማሃማ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኮትዲቯር ምክትል ፕሬዚዳንት ቲዬሞኮ ሜይሊየት ኮኔን ጋር ተወያዩ::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኮትዲቯር ምክትል ፕሬዚዳንት ቲዬሞኮ ሜይሊየት ኮኔን ጋር መወያየታቸውን አስታወቁ። መሪዎቹ በዛሬው ዕለት ባካሄዱት ውይይት፣ በአኅጉራዊ እና የሁለቱ ሀገራት የወል ፍላጎቶች በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ይህ የሁለቱ መሪዎች ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ከሚገኘው 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን የተከናወነ መሆኑ ታውቋል።

Read More