ኢትዮጵያ 39ኛውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት ማስተናገዷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ብሔራዊ የዝግጅት ኮሚቴ ሰብሳቢና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በሰጡት መግለጫ፤ ጉባኤው የኢትዮጵያን የላቀ የመስተንግዶ አቅም፣ አስተማማኝ የጸጥታ ሁኔታና ጨዋነት የተሞላበት የእንግዳ ተቀባይነት ባህል በተግባር ያስመሰከረ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ ስኬት ሊመዘገብ የቻለው በሕዝባችን ትዕግሥትና እንግዳ ተቀባይነት፣ በጸጥታና ደህንነት መዋቅሩ ንቃት፣ በመንግሥት ልዩ ትኩረት እንዲሁም በሚዲያ አካላት፣ በዲፕሎማቶች፣ በበጎ ፈቃደኞችና በሁሉም የብሔራዊ ኮሚቴ አባላት የተቀናጀ ጥረት መሆኑን ጠቁመዋል።
ሁነቱ ኢትዮጵያ የመስተንግዶ አቅሟን እንድታሳድግ ዕድል ከመስጠቱ ባሻገር፣ የሀገራችንን በጎ ገጽታ ለዓለም ያስተዋወቅንበት ነበር ብለዋል አምባሳደሩ፡፡
ጉባኤው በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በሙሉ አምባሳደሩ ምስጋና አቅርበዋል።


