የመንግስት ኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን አብይ የስራ ሂደት ተግባርና ኃላፊነት
- የሂደቱን አመታዊ ዕቅድና በጀት ያዘጋጃል፣ ሲፀድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤አፈፃፀሙንም ሪፖርት ያደርጋል፤
- የአስተዳደሩ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ስራን በበላይነት ይመራል፣ያስተባብራል፤
- የአስተዳደሩ የኢንፎርሜሽን ዋነኛ ምንጭ በመሆን ያገለግላል፣በልዩ ልዩ መንገዶች ያሰራጫል፣በዋና ዋና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ የመንግስትን አቋም ይገልፃል፡፡
- ብሄራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችሉና የአስተዳደሩን መልካም ገፅታ የሚያጎለብቱ ፕሮግራሞችን እንዲዘጋጅና እንዲሰራጩ ያደርጋል፡፡
- ለሚዲያ የኢንፎርሽን ጥያቄ አግባብ ባላቸው የመንግስት አካላት ምላሽ እንዲሰጥ ያደርጋል፤ ዋና ዋና ሃገራዊ ጉዮችና ክንውኖች ተገቢውን የሚዲደያ ሽፋን እንዲሰጣቸው ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
- ልዩ ልዩ የሕትመትና የኦዲዮቪዲዮ ምርቶችን ያመርታል፣የአስተዳደሩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የፎቶ ግራፍና የኦዲዮቪዲዮ ቀረፃ፣የአርማና የህትመት ዲዛይን እንዲሰራላቸው ሲጠይቁ የማዘጋጀትና የማማከር አገልግሎት ይሰጣል፣
- የመንግስት ፖሊሲዎችን ለማስተዋወቅና ለገጽታ ግንባታ የሚረዱ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራም ያዘጋጃል የአስተዳደሩ መስሪያ ቤቶች እንዲሰራላቸው ሲጠይቁ ያዘጋጃል ፣ ያማክራል፣
- በአስተዳደሩ ለሚገኙ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገራት ጋዜጠኞች እንደ አስፈላጊነቱ መግለጫዎችን ይሰጣል፣
- አስተዳደሩ ሊታወቅበት በሚገባው ትክክለኛ ገጽታ እንዲታወቅ ሰፊ መረጃ ይሰጣል ፣ በአስተዳደሩ ላይ የሚሰነዘሩ የተሳሳቱ መረጃዎች ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣
- ዓላማውን ለማሳካት የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡


