- የቢሮው ተልዕኮ
ተልዕኮችን «አስተማማኝ የመንግስት መረጃ ልውውጥን በማስፈን ፣ በሙያ ክህሎቱ የዳበረና በከፍተኛ ስነ-ምግባር የታነፀ የኮሙዩኒኬሽን ልማት ሠራዊት በማፍራት ፣ ስትራቴጂያዊ አመራር በመስጠት መረጃን መሰረት ያደረገ ተሳታፊ ህዝብ ፣ የጋራ መግባባት የሰፈነበት ፣ በጎ ገፅታ ጎልቶ የወጣበትና የፈጣን ምላሽ አሰራር ያዳበረ አስተዳደር እውን ማድረግ ነው፡፡
- የቢሮው ራዕይ
<< በ2012 በጠንካራ የኮሙዩኒኬሽን ልማት ሠራዊት የታገዘ አስተማማኝ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ተፈጥሮ ማየት፡፡ >>
- የቢሮው እሴት
- በዕውቀትና በሙያ ብቁ ሆኖ መገኘት፣
- የመረጃ ኃይል ሆኖ መገኘት፣
- ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
- ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነትን አምርሮ መታገል፣
- ለዕድገትና ብልፅግና መስራት፣
- ለሥርዓተ ፆታ ስኬታማነት በጽናት መስራት፣
የቢሮው ስልጣንና ተግባር
ቢሮው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡
- የአስተዳደሩ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ስራን በበላይነት ይመራል፣ያስተባብራል፤
- የአስተዳደሩ የኢንፎርሜሽን ዋነኛ ምንጭ በመሆን ያገለግላል፤ በልዩ ልዩ መንገዶች ያሰራጫል፤ በዋና ዋና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ የመንግስትን አቋም ይገልፃል፤
- የአስተዳደሩን ሴክተር መስሪያ ቤቶችን የሕዝብ ግንኙነት ስራ አቅጣጫን ያስቀምጣል፤ ያስተባብራል፤
- ብሄራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችሉና የአስተዳደሩን መልካም ገፅታ የሚያጎለብቱ ሁነቶችን ይፈጥራል፤ ያስተባብራል፤ ያስተዋውቃል፤ በነዚህ ተግባራት ላይ የሚያተኩሩ የሚዲያ ፕሮግራሞች እንዲዘጋጁና እንዲሰራጩ ያደርጋል፤
- በአስተዳደሩ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን እንዲሁም በብሄራዊ መግባባት እና በገፅታ ግንባታ ስራዎች ከሴክተሮች፣ ከቀበሌዎች፣ ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የግንኙነት ስርዓት ይዘረጋል፤ ተፈፃሚነቱን ይከታተላል፤
- የአስተዳደሩ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና ወረዳዎች የሕዝብ ግንኙነት ሠራተኞችን የአቅም ግንባታ ተግባሮችን ያከናውናል፤ የሰራተኞቹንም ምልመላና ቅጥር በተመለከተ አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፤
- የሚዲያ ሞኒተርኒግ፣ የፕሬስ ዘገባ፣ የከባቢያዊ ቅኝት ስራዎችን ያከናውናል፤ ትንተና ያዘጋጃል እንዲሁም የህዝብ አስተያየት ያሰባስባል፤
- ሚዲያዎች ከአስተዳደሩ ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት ያስተባብራል፤ ለሚዲያ ኢንፎርሜሽን ጥያቄ አግባብ ባላቸው የመንግስት አካላት ምላሽ እንዲሰጥ ያደርጋል፤ ዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ክንውኖችና ሁነቶች ተገቢው የሚዲያ ሽፋን እንዲሰጣቸው ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
- በመንግስት ፖሊሲዎችና በተለያዩ አስተዳደራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለመስጠትና ግልፅነትን ለመፍጠር ሕዝባዊ የውይይት መድረኮችን ያዘጋጃል ያስተባብራል፤
- ከፍተኛ የአስተዳደሩ ባለስልጣናት ህብረተሰቡን በአካል አግኝተው እንዲያነጋግሩና ተቋማትን ፣ድርጅቶችን ፣ሁነቶችን፣የስራ አፈፃፀሞችንና ክንውኖችን እንዲጎበኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
- ልዩ ልዩ የሕትመትና የኦዲዮቪዲዮ ምርቶችን ያመርታል፤ የአስተዳደሩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የፎቶ ግራፍና የኦዲዮቪዲዮ ቀረፃ፣የአርማና የህትመት ዲዛይን እንዲሰራላቸው ሲጠይቁ የማዘጋጀትና የማማከር አገልግሎት ይሰጣል፤
- ለንግድ አላማ የሚታተምም ሆነ የንግድ ዓላማ ለሌላቸው ስርጭታቸው በአስተዳደሩ ብቻ ለሆኑ ጋዜጦችና መጽሔቶች የሙያ ፍቃድ ይሰጣል፤ በሕጉ መሰረት መሰራታቸውን ይከታተላል፤
- የማስታወቂያ የስራ ህግን ተከትሎ ለአስተዳደሩ እና ለሀገር ልማት አስተዋፅኦ ሊያደርግ በሚችልበት አቅጣጫ ስለመከናወኑ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፤
- በአስተዳደሩ ውስጥ በቋሚ የዜና ወኪልነት ለሚመደቡ የውጭ አገር እና የአገር ውስጥ የዜና ወኪሎች ፍቃድ መውሰዳቸውን ያረጋግጣል፤ ህግ አክብረው መስራታቸውን ይከታተላል፤
- የመንግስት ፖሊሲዎችን ለማስተዋወቅና ለገጽታ ግንባታ የሚረዱ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራም ያዘጋጃል የአስተዳደሩ መስሪያ ቤቶች እንዲሰራላቸው ሲጠይቁ ያዘጋጃል ያማክራል፤
- በአስተዳደሩ ለሚገኙ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገራት ጋዜጠኞች እንደ አስፈላጊነቱ መግለጫዎችን ይሰጣል፤
- አስተዳደሩ ሊታወቅበት በሚገባው ትክክለኛ ገጽታ እንዲታወቅ ሰፊ መረጃ ይሰጣል፣በአስተዳደሩ ላይ የሚሰነዘሩ የተሳሳቱ መረጃዎች ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- በኮሙዩኒኬሽን ስራ ዙሪያ በሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ ወገኖች መካከል በጋራ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ የአጋርነት ስርዓት ይዘረጋል፤
- ዓላማውን ለማሳካት የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡


