የአረጋውያን ቀን “ወቅታዊና ተግባራዊ ምላሽ ለአረጋውያን” በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ ተከብሯል።
የአረጋውያን ቀን በአል በአለምአቀፍ ለ30ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ29ኛ ጊዜ የተከበረ ሲሆን በድሬዳዋም በፓናል ውይይትና በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል። በበአሉ ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አህመድ ቡህ “አረጋውያን ሕያው ሰበአዊ ቅርስና የማህበራዊ ኑሮ ምሶሶ በመሆናቸው በህይወት ዘመናቸው ያካበቱት ከፍተኛ እውቀትና ልምድ ለተተኪው ትውልድ በአግባቡ እንዲሻገር አዲሱ ትውልድ አረጋውያንን በፍቅር እየተንከባከበ በአክብሮት ሊያዳምጣቸውና ሊታዘዛቸው ይገባል” ብለዋል።…


