በድሬዳዋ አስተዳደር ለ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ድሬዳዋን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤት የሚመለመሉ እጩዎች፣ ለአስተዳደሩ ምክር ቤት እና ለቀበሌ ምክር ቤት እጩዎች ተመልምለው ቀርበዋል።
ለተወካዮች ምክር ቤት፣ ለአስተዳደሩ ምክር ቤትና ለቀበሌ ምክር ቤት የተመለመሉ እጩዎች መስፈርቱን መሰረት በማድረግ ከተማና ገጠርን ባማከለ መልኩ የተመለመሉ ሲሆን ለተወካዮች ምክር ቤት 2 እጩዎች፣ ለከተማ ምክር ቤት 189 እጩዎች እና ለቀበሌ ምክር ቤት ለእያንዳንዱ ምክር ቤት 300 እጩዎች በመመልመል ለሶስቱ ምክር ቤት የብልጽግና ፓርቲ ተመራጭ እጩዎች በፓርቲው የቀበሌ አስተባባሪዎች፣ በአስተዳደሩ አስተባባሪዎችና በመሠረታዊ ድርጅትና ህዋስ አመራሮች እጩዎችን የማስተቸት ስራ በመስራት ማስተካከያም በማድረግ እጩ ተመራጮች ተመልምለዋል።
አጠቃላይ ሁኔታው በአስተዳደሩ ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ ቀርቦ በቀጣይ ሶስቱ ምክር ቤቶች የምሁራን ስብስብ ያለበት፣ ለወጣቶች ልዩ ትኩረት የሰጠና የሴቶች ተዋጽኦ የጠበቀ መሆኑን የገለጹ ሲሆን በመጨረሻም ሰፊ ውይይት በማድረግ እጩዎችን ለማጽደቅ ተችሏል።
በመድረኩ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የመምሪያ ኃላፊዎችና የሊግ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች የከተማና የገጠር አመራሮች ተገኝተዋል።
ምንጭ፦ DDPP


