በድሬዳዋ አስተዳደር ከኒትባ የተመራ ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፖትርያርክ ጎበኙ።

    በክቡር ከንቲባ የተመራው የድሬደዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፖትርያርክ በመገኘት በፀጥታ አካላት እና አመራሩ እየተጠናከረ የመጣውን መልካም ግንኑኝነት ለማጠናከር የጋራ መድረክ አካሄዱ።
    ልዑካኑ በቤተክርስቲያኒቱ እየተካሄዱ ያሉትን የልማት ስራዎችም ለመጎብኘ ችለዋል።
    ይህ የምክክር መድረክ በከተማ መስተዳደር ደረጃ በአይነቱ የመጀመሪያ እንደሆነ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የተገለፀ ሲሆን ብፁዕታቸውም ለከተማ አስተዳደሩ አመራር እና የፀጥታ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።