መልዕክተ ድሬ 706

    ‹‹በማወቅ ውስጥ አለማወቅ አለ››

    በውበት ውስጥ አስቀያሚነት፤ በአስቀያሚነት ውስጥ ውበት ሊኖር ይችላል። ሰው መመራመር የሚኖርበት የሚኖርባትን ዓለም በጥልቀት ለማወቅ ነው። የሚመራመር ከሩቅ የሚፈለገው መድኃኒት ከዚሁ ከቅርብ ሊያገኝ ይችላል። አለማወቅ በእኛና በምንፈልገው ነገር መካከል ጥቁር መጋረጃ ይሰራል።

    የአንድ ነገርን የዛሬ ምንነት እንጂ ነገ ስለሚሰጠው ዋጋ አናስብም። ሰው ወርቅን በወርቅነት ሳያውቀው ለረጅም ጊዜ ኖሮአል። የሚጠቅም ማዕድን ሆኖ ከመታወቁ በፊት የማይጠቅም የድንጋይ ክምችት ሆኖ ሲታይ ቆይቷል። ብዙ መልካም ነገሮች በራሳችን ውስጥ አሉ። ባለማወቅ ግን ከውጭ እንፈልጋቸዋለን። ከውጭ የምንፈልገውን መልካም ነገር ማግኘት የሚያስችል አቅም በውስጣችን ያለው መልካም ነገር ነው። ሁሉም ሰው አእምሮአዊ፤ መንፈሳዊና አካላዊ አቅሙን በአግባቡ ከተጠቀመ ብዙ ችግር አይፈጠርም፤ ቢፈጠርም በቀላሉ መፍትሔ ያገኛል። በውስጣችን ያለውን መልካም ነገር መጠቀም ስንችል ከውጭ ያለውን ማግኘት አይከብድም። ከውስጥ ያለውን ሳንጠቀም ከውጭ ማግኘቱ ግን ቀላል አይሆንም። ወጣቶች ይህን እውነት መረዳት አለባቸው፡፡ … ይቀጥላል …ለበለጠ መረጃ ገፅ 2 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 0 6

    መንግስትን በመታዘዝ፣ የጤና ባለሙያዎችን ምክር በማዳመጥ እና

     የሀይማኖት አባቶችን በመስማት አንድነታችንን ስናጠናክር 

    ኮረናን መከላከል እንችላለን

    የኮሮና ቫይረስ በሽታ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተው ትልቅ እና በቢሊየን የሚቆጠሩ ህዝቦች ባላት  በቻይና ውስጥ በምትገኘው ኡዋን ግዛት ነው፡፡  የወረርሽኝ በሽታው ከሰው ወደ ሰው የመዛወር ባህሪው ቻይናዊያንን በሙሉ በእጅጉ ያስደነገጠ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የቻይና ህዝብ ቶሎ ተስፋ የማይቆርጥ እና ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ተላላፊ በሽታዎች ልምድ የቀሰመ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ድህነትን በመሳሰሉ ሌሎች ችግሮች ላይ በአንድ ልብ እና በአንድ ሃሳብ በመዝምት ድል ነስቷል፡፡

    ባላቸው ልምድ ተጠቅመው መንግስት እና ህዝብ በመደማመጥ እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችን ምክር  በመቀበል  ጠንካራ አንድነት ያለው አቋም በመያዝ በኮሮና ቫይረስ በሽታ ላይ በከፈቱት የጋራ ዘመቻ የበሽታውን ጉልበት በመስበር አሁን ወደ ድሮው ሠላም ተመልሰዋል፡፡ ከዚያም አልፈው በሽታው የበረታባቸውን ሀገሮች ለመርዳት እንደ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ ካሉ ሀገሮች ጎን በመሰለፍ ልምዳቸውን በተግባር እያሳዩ ነው፡፡ … ይቀጥላል …ለበለጠ መረጃ ገፅ 3 ያንብቡ  መልዕክተ ድሬ7 0 6

    ዘመናዊው የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ የመጨረሻ የግንባታ ምዕራፍ ላይ ደርሷል

    ሀገራችን ኢትዮጵያ በስፖርቱ ውስጥ የቆየ ታሪክ ቢኖራትም በውጤት ረገድ ግን ከሩጫው ውጪ
    ባሉ የስፖርት አይነቶች የቆይታዋን ያህል ውጤታማ አይደለችም። ይሄን ታሪክ ለመቀየር በመንግስት ትኩረት ተሰቶ ከተሰሩ ስራዎች መሀከል የስፖርት አካዳሚዎችን ማስፋፋት ተጠቃሽ ነው።

    የስፖርት አካዳሚዎች የቋቋሙበት ዋና ዓላማ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች በመመልመል እና ሳይንሳዊ ስልጠና በመስጠት በአህጉር እና ዓለም የውድድር መድረኮች ሀገራችንን የሚወክሉ እና ውጤት የሚያስመዘግቡ ስፖርተኞችን ለማፍራት ነው፡፡
    በድሬዳዋ አስተዳደር ከ 292 ሚሊየን ብር በላይ እየተገናባ የሚገኘው የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፓርት አካዳሚ ከፍፃሜው ሊደርስ ተቃርቧል። ሁለት መቶ ዘጠኝ ሺ ሁለት መቶ ካሬ ሜትር የሚሸፍነው አካዳሚው በ 14 የስፖርት አይነቶችን ወጣቶችን ተቀብሎ ማስተናገድ ይችላል። … ይቀጥላል ..ለበለጠ መረጃ ገፅ 12 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 0 6