መልዕክተ ድሬ 705

    ብሩህ ተስፋችንን በጋራ ለማየት 

    ተደጋግፈን እንቁም ያለመዘናጋት

    በእጅጉ አስጊ፤ እንዲሁም ለሌሎች አሸባሪ የሆኑ እብሪተኛ ወራሪዎች እና ታሪካዊ ጠላቶቻችን የተሰነዘረብንን አደገኛ ጥቃት አክሽፈን ተሻግረን እዚህ ደርሰናል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም በሚሊየኖች የሞቆጠሩ የዓለምን ህዝብ የፈጁ ተዛማች በሽታዎች እና የረሃብ እና የድርቅ አደጋ ተሻግረን ዛሬን ማየት ችለናል፡፡ ለዚህ ሁሉ ስኬት እና የመሻገር ድል  ለልዩነቶቻችን ቅድሚያ ሳንሰጥ በመደማመጥ እና በጋራ በመቆም ችግሮቹን ተጋፍጠን ያሸነፍንብት የአንድነት ኃይላችን ነው፡፡ እስካሁን ድረስ በዚህ በመደማመጥ እና በጋራ በመቆም ጠንካራ ኣንድንታችን ፊት ቆሞ ያሸነፈን ችግር የለም፡፡ ለዚህ ደግሞ ዓለም መቼም ቢሆን የማይረሳው አስገራሚ ታሪካችን ምስክር ነው፡፡

    በሉዓላዊነታችን፣ በህልውናችን እና በጠንካራ አንድነታችን ላይ የመጡብንን የውስጥ እና የውጪ ችግሮች ብሎም ስጋቶችን በድል ተሻግርናል፡፡ እዚህ የደረስነው የጋራ የሰብዐዊ ክብር መኖሪያችን ለሆነችው ሀገራችን ብሎም ለወገኖቻችን ያለን ፍቅር ጠንካራ በመሆኑ ነው፡፡ ትእቢተኛ እና እብሪተኛ ወራሪዎችን ያሳፈረው እና ያልተረዱትን ማንነታችንን በሚገባ ተረድተው ሽንፈታቸውን በመቀበል እንዲያከብሩን ያደረገው ለሀገር እና ለወገን ካለን ጠንካራ ፍቅር በሚመነጨው ወኔያችን ነው፡፡ …ይቀጥላል…ለበለጠ መረጃ ገፅ 3 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 0 5

    ያልታከመው መጥፎ በሽታ

    እጅ መንሻ ይሉታል ቀደምት የኛዎቹ አበዎች ስሙን ሸፈንፈን ሲያደርጉት ትናንትናን ባህል በመሰለ መልኩ እግሩን እያስረዘመ ተራምዶ ዛሬን ዘመናዊ ሌብነት የሆነው ሙስና፡፡ ወደ አንድ ሀገረ ገዢ አሊያም የጭቃ ሹም ዘንድ ለአቤቱታ አሊያም ለተለያዩ ጉዳዮችና የወደደም ነገን በአንዳች ገጠመኝ የበላዮቼ ፊት ብቆም ብሎ ከወዲሁ ቀብድ መሰል ቅደመ ፊት ማሳያ እነሆኝ ይላል፡፡ ሁሉም ግን ስሙን እነዲህም እንዲያም ይበሉት የዚህ ሁሉ ስያሜው ዛሬ ላይ ሙስና ብለን የምንጠራው ስያሜ ያላቸው አካሄዶች ናቸው እነዚህ ስጦታዎች፡፡ በርካታ ወቅታዊ ጉዳዮቻችን ተይዘን ችላ ያልነው ትናንትናም ይሁን ዛሬ ወቅታቂ ጉዳያችን ላይ ትኩረቱን ያደረገውና እኔም ከዚህም ከዛም ካገኘሁትና የኔም ከምለው የፃፍኩትን ታነቡ ዘንድ ጋበዝኳችሁ፡፡ ….ይቀጥላል….ለበለጠ መረጃ ገፅ 4 መልዕክተ ድሬ7 0 5

    የአምባ ገነኖች የስልጣን ጥም አባዜአቸውና የማያምር መጨረሻቸው

    ዛሬ በአለማችን ላይ መንግስታቶች ሲመሩት እና ሲያስተዳድሩት ባለው እና  በነበረው ሕዝብ ላይ  የሰብአዊ መብት ረገጣ እስራት እና ግድያ በሕዝባቸው ላይ እንደሚያደርሱ ይታወቃል፡፡ በተለይም የአፍሪካ መሪዎች እና መንግስታቶች በአንባገነንት  የሕዝባቸውን ሰብአዊ መብት በመርገጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ አገራችን ኢትዮጵያ አንዷ ናት :: ከለውጡ በፊት በሀገራችን ኢትዮጵያ በስልጣን ላይ የነበረው መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ አይን ያወጣ የሰብአዊ መብት ጥሰት በዜጎች ላይ እየፈጸመ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ይህም የወያኔ የዜጎችን የሰብአዊ መብት መርገጥ እና ሕዝብን እያስፈራሩ ረግጦ መግዛት ከምንም ነገር የመነጨ ሳይሆን ሕዝቡ ስለ ዜግነት መብቱ እንዳያስብ በታጠቀ ኃይል እያስፈራሩ የሥልጣን እድሜን ለማራዘም ወያኔዎች ያዋጣናል ብለው የመረጡት መንገድ ሲሆን ዜጎችን መረበሽ፣መዝረፍ፣ማሰር እና መግደልን ተያይዘውት ይገኛሉ:፡  … ይቀጥላል…ለበለጠ መረጃ ገፅ 10 መልዕክተ ድሬ7 0 5