የተመዘገበውን አስገራሚ ድል አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል
አብረን በኖርንባቸው ባለፉት አያሌ ዓመታት ያካበትናቸው የመቻቻል፣ የአብሮነትና በሀገር ጉዳይ ላይ የአትንኩን ባይነት እሴቶቻችንን በየጊዜው ልናድሳቸውና ለመጪው ትውልድ በአደራ ልናሻግራቸው ይገባል፡፡ እነዚህና ሌሎችም እሴቶቻችን በፍቅር፣ በይቅርታ እና በመደመር የሚገነባውን ጠንካራ አንድነታችንን የበለጠ የማጠናከር ኃይል ስላላቸው የአሁኑ ትውልድ ትምህርት ሊወስድባቸው ይገባል፡፡
ለመሆኑ የመከላከያ ሠራዊታችን ብሄር፣ ዘር፣ ቀለም፣ ዕድሜ፣ እምነትና ሐይማኖት ወ.ዘ.ተ ሳይለያቸው ሁሉም በሀገር ፍቅር እና ወኔ ሆ— ብለው በክህደት በዘረፈው በዘመናዊ የጦር መሣሪያ እስካፍንጫው ታጥቆና እና በትግራይ ህዝብ ስም በሚነግደው ጁንታው ህወሀት ላይ እንዲንዘምቱ ያደረጋቸው እውነታ ምንድነው? … ይቀጥላል…ለበለጠ መረጃ ገፅ 3 ላይ ያንብቡ መልዕክተ ድሬ704
ጊዜ ሲከዳ
የዚህች ግዙፍ አለም ነዋሪና አደማቂ የሆኑት አውአፍት በክረምት ወራት ተሸማቀውና በየዛፎቹ ላይ ሆነው ቅዝቃሴ ባልገታው የምንቃራቸውን ክፍች እያሰባጠሩ ጩኽታቸውን ተያይዘውታል፡፡
ድንገት ከእንቅልፍ ሲነቃ የመኝታ ክፍሉ ጨለማ ነው፡፡ እነኚህ ሁሌ በዝማሬአቸው መንፈሱን እየሰረቁ የሚማርኩት የንጋት አብሳሪ ወፎችን ድምጽ ሰማ፡፡ አልጋው ላይ እንዳለ የግርግዳውን ማብሪያ ማጥፊያ ተጫነው ከመቅፅበት ቤቱ በብርሃን ተሞላ ወደ ግርግዳው ላይ እተሰቀለ ሰአት ላይ አይኑን እያሻሸ አየ፡፡ ብርሃን ስለአጭበረበርረው በድጋሚ እሸት አደርጎ ሲመለከት 11፡15 ይላል፡፡ ወዲያው ከአልጋው ፈንጠር ብሎ ወርደና ቀልቡን ወደ ሳበው ድምጽ ተመስጦ በፒጃማው ወደ መስኮቱ ሔዶ እያየ የድምጻቸውን ቅላጼ ሲከታተል ቆይቶ ‹‹ወይ የእ/አብሔር ስራ አሁን እኔ አልወቅ እንጂ እነሱ እኮ ተግባብተው እየተነጋገሩ ይሆናል፡፡ይቀጥላል….ለበለጠ መረጃ ገፅ 2 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ704
ላለፉት አስር ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአንደኛ ደረጃ የጤናና የአካል ብቃት የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቋል
ስልጠናቸውን በአግባቡ የተከታተሉ አሰልጣኞችም ተመርቀዋል። በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሻኪር አህመድ የአስተዳደሩን ጥሪ በመቀበል ስልጠናውን ሲሰጡ የነበሩትን አሰልጣኞች በማመስገን ለተመራቂ አሰልጣኞች መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም ተመራቂዎቹ በሰለጠኑት ሙያ በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ ኮሚሽኑ ድጋፉን እንደሚያደርግ ገልፀው፤ አቅማቸውን ለማሳደግም በቀጣይ ሌሎች ስልጠናዎች እንደሚያመቻች ተናግረዋል። ኮሚሽነር ሻኪር አክለውም ስልጠናውን ለመስጠት ያታቀደው ቀደም ብሎ ቢሆንም ከኮቪድ 19 ስርጭት ጋር በተያያዘ መዘግየቱን ገልፀው፤ በቀጣይ ስልጠናውን በማስፋት በማረሚያ ቤቶችና በትምህርትቤቶች ላይ ለመስራት መታቀዱን ገልፀዋል።… ይቀጥላል…ለበለጠ መረጃ ገፅ 12 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ704


