በድሬዳዋ በዘጠኙም ቀበሌዎች የፅዳት የንቅናቄ ዘመቻ የካቲት 06/2013 ይጀመራል፡፡

    በአሰተዳደሩ ዘጠኙም ቀበሌዎች መንደሮችን በመስፈርት በመምረጥ ሞዴል መንደሮችን ለመፍጠር እንዲሁም በተመሳሳይ ለንቅናቄና ለዘመቻ ፅዳት በመስፈርት ለይቶ በመምረጥ የፅዳት ስራዎችን ለማከናወን ከተማ አቀፍ የፅዳት ህዝብ ንቅናቄ በመጪው ቅዳሜ እንደሚጀመር የአስተዳደሩ ፅዳትና ውበት ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ጣሂር ሮብሌ አስታውቀዋል፡፡
    በተጨማሪም በየቀበሌው ክፍት ቦታዎችን በመለየትና የቆሸሹ አካባቢዎችን በማፅዳት የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን ጎን ለጎን ለማከናወን የተጀመሩ ስራዎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ኃላፊው ገልፀዋል፡፡