ባለፉት 6 ወራት 2012 ታቅደው ሲተገበሩ የቆዩና በተለያዩ ችግሮች ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅ ስራዎችን ሲሰራ እንደቆየ ተገልጽዋል፡፡
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አብዱልጀዋድ መሐመድ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት ጽ/ቤቱ በከተማዋ የመሠረተ ልማት ግንባታ እና ማስፋፋት እንዲሁም ማዘጋጃ ቤታዊ አገለግሎት አሰጣጥን ለከተማዋ በሚመጥን መልኩ አገልግሎት ለመስጠት ባለፉት 6 ወራት ትኩረት ሰተው ሲተገብሩ መቆየታቸውን ገልፀዋል፡፡
የከተማዋን መሠረተ ልማት ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን የመንገድ፣ የውሃ፣ የቄራ ፣አረንጓዴ ልማት እረገድ ተጠናክረው እየተሰሩ መሆናቸውን ሃላፊው አክለው ገልጸዋል፡፡ ባለፈው በጀት አመት ተጀምሮ ለዘንድሮ አመት ሳይጠናቀቁ የተሻገሩ የገጠር መንገዶች፣ የኮብልስቶን መንገድና ከመንገድ ግንባታ ተጠናቀው አገልግሎት እንዲሰጡ ዝግጁ ሆነዋል ብለዋል፡፡
አያይዘውም ቁጥር ሁለት አፍሪካ ድልድይ ግንባታ የተለያዩ ችግሮች የነበሩት እንደነበር በመጠቆም ችግሮቹን በመቅረፍ ግንባታው እንዲጀመር ተደርጓል ብለዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በክረምት የተጎዱ የጎርፍ መከላከያዎች ጊዜያዊ ጥገና እንደተደረገላቸው መሆኑን በመግለፅ የመንገድ የመሠረተ ልማት ጥገና ለማከናወን ቀደም ሲል የነበረውን ችግር ለመቅረፍ በአስተዳደሩ የጥገና ማሽን መገዛቱ በቀጣይ በራሳስ አቅም ለመጠገን ያስችለናል ብለዋል፡፡
ከውሃ ጋር ተያይዞ ያለውን ምርት ለማሳደግ ሶስት ጉድጓዶች ቁፋሮ መደረጉን በ6 ወር ውስጥ 1500 አዲስ የውሃ መስመር ዝርጋታን ለማከናወን ታቅዶ 1700 በመተግበር ከእቅድ በላይ ማከናወናቸውን ገለጸዋል፡፡
የህብረተሰቡን የቄራ አገልግሎት ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ዘመናዊ ማቀነባሪያ ያለውና በቀን ከ3ሺ በላይ እንሰሳቶችን ለእርድ የሚያውል በኤሌክትሪክ ማሽን የሚንቀሳቀስ አዲስ ቄራ ተገንብቶ ወደ ስራ ለማስገባት ማሽኑን የሚያንቀሳቅስ ባለሙያ ባለመኖሩና እራሱን የቻለ የገበያ ጥናት በማስፈለጉ የዘገየ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ባለፉት 6 ወራት እቅድን ከመፈጸም አኳያ ዘርፉ የሚጠይቀውን አመራርና ባለሞያ አለመኖር እንዲሁም የበጀት እጥረት እቅዱን በተሟላ መልኩ ለመፈፀም ተግዳሮች እነደነበሩ ገልጸው በቀጣይ ችግሮቹን ለመቅረፍ እንዲቻል የሰው ኃይል የቅም ግንባታና የለውጥ ስራዎች ላይ ትኩረት ሰተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡


