የአፍረን ቀሎ የሙዚቃ ቡድን የመጀመሪያውን ሀገር አቀፍ የባህል ፌስቲቫል ላይ ትርዒት ያሳየበትና ባንዱን የመሠረተበት በድሬዳዋ ምድር ባቡር ክለብ ግቢ ውስጥ የሚገኘውን ቤት ለበርካታ ዓመታት ያለስራ ተዘግቶ የቆየ በመሆኑ ታሪካዊ ይዘትና ቅርጹን ሳይቀይር ታድሶ ነው የተመረቀው ፡፡
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጀሃር ፣ ምክትል ከንቲባ አቶ አርቢ ቡህ ፣ የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ፣የአስዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የአፍረን ቀሎ የሙዚቃ ቡድን መስራች የሆኑት አርቲስት ኡስማኤል ሙመድ አደም እና ከካናዳ ፣ጀርመን፣ አውስትራሊያና አሜሪካ የመጡ በሙዚቃ ቡድኑ ውስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩ የቀድሙ የቡድኑ አባላት እና የባህል እንቅስቃሴውን ዳግመኛ እንዲያንሰራራ በቀድሞው ስያሜ አፍረን ቀሎ ጥላ ስር የተደራጁ ተተኪ ወጣት የባህል ቡድኑ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከናውኗል ፡፡
ይህ የአፍረን ቀሎ የሙዚቃ ቡድን የመጀመሪው ትርዒት የታየበትና ባንዱ የተመሠረተበት ቤት ዳግመኛ ታድሶ አገልግሎት ላይ እንዲውል መደረጉ የሙዚቃ ቡድኑ አባላት በዚያ ምቹ ባልነበረና አስቸጋሪ በሆነ ወቅት ባህልና ቋንቋውን ለማሳደግ ያለፉባቸውን ፈታኝ የታሪክ ውጣ ውረዶችና እንግልት ፣የከፈሉትን ውድ ዋጋ ለመዘከርና ለተተኪ ወጣት የባህል ቡድን አባለትን እና ከያኒያን ለማፍራት ለኪነጥበብ እድገት ያለው አስተዋጾ የጎላ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡


