የድሬደዋ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ከሰአት በኋላ ባካሄደው ስብሰባ ውሳኔ አስተላልፏል

የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የ12 ክፍል ፈተና እና በአሸዋ በደረሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ተመልክቶ ውሳኔዎችን አሰተላልፏል፦

1ኛ :- የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ በኦን ላየንና በወረቀት ለማሕበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 3 እስከ 5፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ ከሐምሌ 9 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ለሚሰጠው ፈተና በአስተዳደሩ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲጠናቀቅ ውሳኔ አሳልፏል።

2;-በድሬዳዋ ማክሰኞ ሰኔ 25/2016 ዓ.ም አሸዋ የገበያ ቦታ ላይ በደረሰው የእሳት አዳጋ ጊዜያዊና ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት አብይ ኮሚቴና በስሩ አምስት ንዑሳን ኮሚቴዎችን የተቋቋሙት ለተጎጂዎች ማረጋጋት ፣ የጉዳት ልየታና መልሶ ማቋቋም እንዲሁም ንዑስ ኮሚቴው የንብረት ጉዳትን በአይነት ፣ በብዛትና በገንዘብ ተመን መለየት እንደዚሁም ጊዚያዊ የገበያ ስፍራ ምችችት የተጀመሩ ስራዋች ላይ በመወያየት ኮሙቴው እየሰራ ያለው ስራዋች በየሦስት ቀናት እየተገመገመ የታቀዱ እቅዶ በፍጥነት እንዲሰሩ ውሳኔ አሳልፏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *