የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር በአስተዳደሩ በስፋት እየተተገበረ መሆኑ ተገለፀ

በድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ሊግ አስተባባሪነት የሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እንዲሁም የሴቶች አደረጃጀት በጋራ በመሆን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር በዛሬው እለት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሪፈራል ሆስፒታል ቅጥር ጊቢ ውስጥ አከናውነዋል

በዚሁ መርሀ-ግብር ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ\ሮ ፈቲህያ አደን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር በድሬዳዋ አስተዳደር በስፋት እየተተገበረ መሆኑን ተናግረው በተለያዩ ጊዜያቶች በከተማዋ ላይ የሚተከሉትን ችግኞች በዘላቂነት ተንከባክቦ ማፅደቅ እንደሚገባም ነው ክብርት ወ\ሮ ፈቲህያ አደን በእለቱ የተናገሩት ።

እንደ ሀገር ብሎም በድሬዳዋ አስተዳደር ላይ እየተካሄደ ያለውን የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር ለማስቀጠል በተለይም የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ሊግ በርካታ ስራዎችን እየተሰራ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ሊግ ኃላፊ ወ\ሮ ኢፍቱ አህመድ ተናግረዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *