“በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ዓሻራችንን እናኑር”፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ዓሻራችንን እናኑር ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በአንድ መንፈስ በመላው ኢትዮጵያ ዓሻራችንን እናኑር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንድ ከሆን ከዚህም በላይ እንችላለን! ሲሉ ገልፀዋል።

አዋቂዎች ከ20 በላይ፣ ታዳጊዎች ከ10 በላይ ችግኞችን በመትከል ለሀገር ያለንን ፍቅር፣ ለትውልድ ያለንን ስጦታ በተገቢው ስፍራ እንግለጥ ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *