የሰቆጣ ቃል ኪዳን የሀገር በቀል መፍትሔ ውጤታማ ማሳያ መሆኑ ተገለፀ::

የሰቆጣ ቃል ኪዳን የመቀንጨር ችግርን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት በመንግስት ባለቤትነት የሚተገበር፤ የሀገር በቀል መፍትሔ ውጤታማ ማሳያ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት “የኢትዮጵያ ምግብ ሥርዓት ትራንስፎርሜሽን፣ የምግብ እና ሥርዓተ ምግብ ስትራቴጂ እና የሰቆጣ ቃል ኪዳን እንዲሁም የማኀበረሰብ አቀፍ ጤና መድን የ2016 ዓ.ም አፈፃፀም እንዲሁም የ2017 ዓ.ም ዕቅድን ገምግመናል” ብለዋል፡፡

የዜጎችን የምግብ እና የሥርዓተ ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ፣ የጤና መድን አገልግሎትን ለማሳደግ እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦችን ለማገዝ፤ መንግስት፣ መላው ህዝብ እና አጋር አካላት ሐብት በማሰባሰብ እና በውጤታማነት አሟጦ በመጠቀም ላይ በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም የሰቆጣ ቃልኪዳንን ከሌሎች ሀገር በቀል ንቅናቄዎች ጋር አስተሣሥሮ መተግበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የጋራ አቅጣጫ መቀመጡን፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *