የድሬዳዋ “ደረቅ ወደብ በመልቲ ሞዳል አገልግሎት ባለፉት 3 ወራት 334 ኮንቴነር ማስተናገዱን እና በተያዘው ሩብ አመት 21 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለፁ ።

የድሬዳዋ “ደረቅ ወደብ ” በቀን ከ2400 በላይ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ያስተናግዳል ::

ደረቅ ወደቡ በመልቲ ሞዳል አገልግሎት በያዝነው ሩብ አመት 334 ኮንቴነር ማስተናገድ መቻሉ ተገልጿል። በዚህም በሩብ አመቱ ከአገልግሎት 21 ሚሊየን ብር ትርፍ ማግኘቱን የድሬዳዋ ደረቅ ወደብ አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል ::

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የድሬዳዋ ደረቅ ወደብ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም ታደለ እንደገለጹት የድሬዳዋን ነፃ የንግድ ቀጣና ለማሳለጥ የተገነባው ዘመናዊ ደረቅ ወደብ ዛሬ ላይ 2ሺ 400 የጭነት ተሽከርካሪዎችን እያስተናገደ መሆኑን ተናግረዋል:: አብዛኛዎቹ የገቢና ወጪ እቃዎች የምግብ ፍጆታ ምርቶች መሆናቸውን ገልጸው መንግስት በልዩ ሁኔታ በፈቀደው መሠረት ከጅቡቲ ወደብ ላይ የነበሩ በነዳጅ የሚሰሩ 2ሺ 6ዐዐ መኪኖች መግባታቸውንና ገብተው በድሬዳዋ ደረቅ ወደብ በኩል መስተናገዳቸውን አቶ ኤፍሬም እንዳለ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የድሬዳዋ ደረቅ ወደብ አገልግሎት ድርጅት ስራስኪያጅ እንዳሉት የድሬዳዋ ደረቅ ወደብ ነፃ የንግድ ቀጣና አቅራቢ መመስረቱ ደንበኞቹን በቅርበት ማግኘት መቻሉ ደረቅ ወደቡን ልዩ ያደርገዋል ሲሉ አክለዋል።

በቀጣናው ከሚሰጠው አገልግሎቶች መካከል አንዱ የአገሪቷን ገቢና ወጪ ንግድ በተሳለጠ ሎጂስቲክስ የአገሪቱን ልማት ትርጉም ባለው መልኩ እየደገፈና ዓላማውን ሊያሳካ የሚችል ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየሰራ ነውም ብለዋል ፡፡

Dire tv

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *