አስተዳደሩ ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የህግ የበላይነት የማስከበር እርምጃው አጠናክሮ ቀጥሏል።
ሰሞኑን በተፈጠረው ረብሻና ሁከት ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ 110 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ላለፉት ሶስት ቀናት በድሬዳዋ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው ሁከትና ብጥብጥ ተሳትፈዋል የተባሉ 110 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የድሬዳዋ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል፡፡ በአስተዳደሩ አንዳንድ አካባቢዎች የተነሳው ተቃውሞ መልኩን ቀይሮ በዜጎች ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል። በተከሰተው ረብሻና ብጥብጥ ዜጎች ህይወታቸው አልፏል፤ በርካቶች…


