የቁሉቢ ገብርኤል የንግስ በዓልን ለማክበር ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚመጡ ምዕመናን እና የበዓሉ ተሳታፊዎችን በፍቅርና በአክብሮት ለማስተናገድ ዝግጅት መጠናቀቁን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ገለፁ።
በየዓመቱ የሚከበረውን የቁልቢ ገብርኤል ንግስ በዓል ምክንያት በማድረግ የድሬዳዋ ነዋሪዎች እና የአስተዳደሩ አመራሮች የበዓሉ ተሳታፊ እንግዶችን የሚቀበሉበት መርሀግብር በአመት ሁለት ጊዜ የሚሰናዱ ሲሆን ለበዓሉ ተሳታፊዎች በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች የማረፊያ ድንኳን በመጣልና ማረፊያ በማዘጋጀት፥ የእንግዶችን ሰላም፣ደህንነት ከነዋሪው ጋር ተቀናጅተው ይጠብቃሉ። በፍቅር በሰላም ተምሳሌት ትንሿ ኢትዮጵያ ተብላ በምትታወቀው ድሬዳዋ ከተማ በተለያዩ የትራንስፖርት አማራጮች ተጠቅመው ወደ ከተማዋ…


