ስነ-ምግባራዊና ቅንጅታዊ አሰራርን በማሳደግ የማህበረሰቡን እርካታ የሚጨምር አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተጠቆመ::
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በአስተዳደር ለሚገኙ ለሴክተር እና ትምህርት ተቋማት የሰው ሀብት ባለሞያዎች እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች “ሙያዊ ስነ- ምግባር ለስነ-ምግባራዊ አገልግሎት አሠጣጥ እና ቅንጅታዊ አሰራር” በሚል ርዕሰ ስልጠና ሰቷል። በዚህም በስልጠና መድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ፌኑስ አብዱልጀባር ስልጠናው የስነ-ምግባር ብልሽቶችን ለመከላከል አቅም የሚፈጥር መሆኑን የተናገሩ ሲሆን፤…


