ወጣቱ በምክኒያት ሊደግፍ በምክኒያት ሊቃወምና ሊያወግዝ ይገባል
በዓለማችን ያሉ ምሁራን አሁን የምንገኝበት ዘመን የመረጃ ዘመን እንደሆነ ይስማሙበታል፡፡ በእርግጥም እጅግ በዘመኑና ከዚህ በፊት ባልነበሩ የቴክኒዮሎጂ ውጤቶች በመታገዝ መረጃዎች ሊገመት በማይችል ፍጥነት ከዓለማችን አንደኛው ጫፍ ወደ ሌላኛው ጫፍ እየደረሱ ነው፡፡ በዚህም ሳቢያ በጣም ግዙፍና ሰፊ የሆነችው ዓለማችን ወደ አንድ መንደር ተቀይራለች፡፡ መረጃ ትልቅ ሀብት መሆኑን ዓለም በተግባር አስኪመለከት ድረስ መረጃዎች ከምንጊዜውም በላይ የኑሮ ዘይቤያችንን…


