በአስተዳደሩ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር እንዳለ ነዋሪዎች ጠቆሙ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መፍትሄ ተበጅቶለታል ብሏል፡፡
በድሬደዋ አስተዳደር የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያየለ መምጣቱን በተለያዩ የከተማዋ ቀበሌዎች ተዘዋውረን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልፀውልናል፡፡ በከተማዋ የሚኖሩ ነዋሪዎች በተለይም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ነዋሪ የሆኑ እንደገለፁት የአገልግሎት ተደራሽነቱም ቢሆን ከቀድሞው የተሻለ ይሁን እንጂ አሁን ድረስ ለሳምንት ያህል የሚጠፋበት ጊዜ እንዳለ በማሪያም ሳይት ኮንዶሚኒየም ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ትዕግስት ተናግራለች፡፡ የድሬደዋ አስተዳደር…


