“የድሬዳዋን የፍቅርና የአንድነት መግለጫ እሴቶች ለመመለስ መረባረብ ይገባል” የድሬዳዋ ምክትል ከንቲባ አህመድ መሐመድ
ለሀገር አርአያ የሆነውን የድሬዳዋን የፍቅር፣ የሰላምና የአንድነት መገለጫ እሴቶች ለመመለስና ሀገር አቀፉን ለውጥ ከዳር ለማድረስ ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አህመድ መሐመድ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ‹‹አንድ ዕድል ለሰላም›› በሚል መሪ ሃሳብ በተኪያሄደው የዛፍ ጥላ ሥር የእርቅ ውይይት ላይ ሀገር አቀፍ ታላቅ ስብዕና የተላበሱ የሀገሪቱ የኪነ ጥበብና የዘርፈ ብዙ ሙያተኞች ተሳትፈዋል፡፡ በውይይቱ ላይ የተሳተፉት…


