ህብረተሰቡ ሰላሙን በማስጠበቅ እርስ በእርስ የመደጋገፍ ባህሉን እንዲያጠናክር ጥሪ ቀረበ።
የድሬደዋ አስተዳደር በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሀይማኖት አባቶች ጋር ወይይት አድርገዋል። በውይይት መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጁሀር ድሬዳዋ ያሳለፍናቸው ወራት በህብረተሰቡና በፀጥታ አካላት ትብብር ብዙ ዋጋ በተከፈለበት መስዋዓትነት ወደ ቀድሞ ሰላሟ መመለሷን በመጠቆም ይህንን ሰላም ሊያደፈርሱ የሚፈልጉ ቀን ከሌት የማይተኙ በሰው ህይወት ቁማር የሚጫወቱ አረመኔ…


