በገጠር እና በከተማ የሚገኙ የወጣት ማእከላትን በዘመናዊ መልኩ የማጠናከር ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን በገጠር በከተማ የሚገኙ ወጣት ማዕከላትን በዘመናዊ መልኩ የተደራጁ እና ለህብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎት ለማሳደግ እንዲቻል 3 ሚሊዮን 500 ሺ ብር ወጪ የተደረገባቸው የተለያዩ የመማሪያና የመገልገያ ቁሳቁሶችን በስጦታ አበርክቷል፡፡ በአስተዳደሩ የወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሻኪር አህመድ በኮሚሽኑ የወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እስክንድር ከ9ኙም የከተማ ቀበሌዎች እና ከአራቱ ክላስተሮች ለተውጣጡ የወጣት ማዕከላት ሀላፊዎች የቁሳቁስ…


