በገጠር እና በከተማ የሚገኙ የወጣት ማእከላትን በዘመናዊ መልኩ የማጠናከር ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

    የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን በገጠር በከተማ የሚገኙ ወጣት ማዕከላትን በዘመናዊ መልኩ የተደራጁ እና ለህብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎት ለማሳደግ እንዲቻል 3 ሚሊዮን 500 ሺ ብር ወጪ የተደረገባቸው የተለያዩ የመማሪያና የመገልገያ ቁሳቁሶችን በስጦታ አበርክቷል፡፡
    በአስተዳደሩ የወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሻኪር አህመድ በኮሚሽኑ የወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እስክንድር ከ9ኙም የከተማ ቀበሌዎች እና ከአራቱ ክላስተሮች ለተውጣጡ የወጣት ማዕከላት ሀላፊዎች የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
    ኮሚሽነር ሻኪር አህመድ አንደገለጹት ይህ ድጋፍ የወጣቶች የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አንዱ አካል ሲሆን በከተማ እና በገጠር የሚገኙ የወጣት ማዕከላትን ከመጽሐፍት ጀምሮ በተለያ ቁሳቁሶች መደገፍ ማስፈለጉን የኮረና ወረርሺኝን ጨምሮ በተለያዩ ምክኒያቶች ከትምህርት እና ከወጣት መአከላት የራቁ ወጣቶች ወደ ትምህርት ለመመለስ እና ከአልባሌ ቦታዎች ተጠብቀው የዕውቀት ባለቤት እንዲሆኑ ለማስቻል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
    ኮሚሽነሩ አክሎም ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀትላል ብለዋል
    የቢዮ አዋሌ ክላስተር ወጣት ማዕከል ተወካይ የሆነው አቶ መሀዲ መሀመድ እንደተናገረው ድጋፉ በገጠር መሰል ድጋፎችን በጉጉት ለሚጠብቁ ወጣቶች ትልቅ ደስታን የሚፈጥር እና ወጣቱን ወደ ወጣት ማዕከላት እንዲሰበሰቡ የሚያደርግ ነው ብሏል፡፡
    ከሪማ መሀመድ ከዋሂል ክላስተር ወጣት ማእከል የተወከለች ሲሆን ድጋፉን በወሳኝ ጊዜ ጊዜ ተደረገ ስትል ገልጻዋለች፡፡
    በዚህ የወጣት ማዕከላትን በግበአት የማጠናከር ድጋፍ የመጻህፍት ፣ የፈርኒቸሮች ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ የተጠረጴዛ ቴኒስ መጫወቻዎች ፣ የወንበር መቀመጫዎች ድጋፍ ተደርጓል፡፡