በድሬዳዋ አስተዳደር በጉጉባ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት 5 መቶ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የተማሪዎች ምገባ ፕሮጀክት ሊጀመር ነው
ኤልኔት ፋውንዴሽን ከድሬዳዋ ልማት ማህበር እና ከድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን 5 መቶ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግና በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኘው በጉጉባ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የሚተገበር የተማሪዎች ምገባ ፕሮጀክት ለማስጀመር የፊርማ ስነ-ስርአት በዛሬው ዕለት አካሄደ፡፡ በመርሀ ግብሩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አሊዪ እንደ ሀገር የደረሰብንን የትምህርት ስብራት ለመጠገን የምገባ ፕሮግራም ከፍተኛ…


