19ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በድሬዳዋ አስተዳደር “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ በተለያዩ መርሀ ግብሮች እንደሚከበር ተገለፀ::
#DGC ህዳር 3/2017 ዘንድሮ “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በአስተዳደራችን በተለያዩ መርሀ ግብሮች እንደሚከበርና የማጠቃለያ መርሀ ግብሩም ህዳር 18/2017 ዓ,ም እንደሚደረግ የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ በዚህም የሴቶች፣ የወጣቶች እንዲሁም የሲቪል ሰርቫንት የውይይት መድረክ እንደሚኖር ወ/ሮ ፈቲያ ገልፀው፤ በዓሉ…


