ኢትዮጵያ የበርካታ ታሪካዊ ቅርሶች እና የጥንታዊ ስልጣኔ መፍለቂያ መዳረሻ ትልቅ ሀገር ናት” በኢትዮጲያ የእንግሊዝ አምባሳደር ክቡር ዳረን ዌልች።
አምባሳደሩ ይህን ያሉት በዛሬው እለት በጥንታዊቷ ሀርላ ከተማ ጥንታዊ መካነ ቅርስን በጎበኙበት ወቅት ነው። አምባሳደሩ በጉብኝታቸውም በቅርቡ በአስተዳደሩ ይፋ የሆነው ከ 6 ተኛ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ረጅም እድሜ ያስቆጠረ ኪነ-ህንጻ በአርኪዮሎጂስቶች በቁፋሮ መገኝቱን ተከትሎ በጥንታዊቷ የሀርላ መንደር የተገነባውን መኖሪያ ቤቶች ፣ የመቃብር ስፍራዎች ፣ መስጊዶች ፣በዘመኑ የነበሩ የኪነ-ህንጻ ጥበቦችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። አምባሳደሩ ዳረን ዌልች የድሬዳዋ…


