አምባሳደሩ ይህን ያሉት በዛሬው እለት
በጥንታዊቷ ሀርላ ከተማ ጥንታዊ መካነ ቅርስን በጎበኙበት ወቅት ነው።
አምባሳደሩ በጉብኝታቸውም በቅርቡ በአስተዳደሩ ይፋ የሆነው ከ 6 ተኛ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ረጅም እድሜ ያስቆጠረ ኪነ-ህንጻ በአርኪዮሎጂስቶች በቁፋሮ መገኝቱን ተከትሎ በጥንታዊቷ የሀርላ መንደር የተገነባውን መኖሪያ ቤቶች ፣ የመቃብር ስፍራዎች ፣ መስጊዶች ፣በዘመኑ የነበሩ የኪነ-ህንጻ ጥበቦችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
አምባሳደሩ ዳረን ዌልች የድሬዳዋ አስተዳደር ባደረገላቸው ደማቅ አቀባበል መደሰታቸውን ገልጸው አክለውም ኢትዮጵያ የበርካታ ታሪካዊ ቅርሶች እና የጥንታዊ ስልጣኔ መፍለቂያ መዳረሻ ትልቅ ሀገር ናት ብለዋል።
በጉብኝታቸውም በጥንታዊቷ ሀርላ ከተማ የኪነ ህንጻ ጥበቦች፣ እምነት ና ሀይማኖት ስልጣኔዎች የተመለከቱ መሆኑን ገልጸው
ኢትዮጵያ የየራሳቸው ታሪክ፣ቋንቋ፣ ባህልና ልምድ፣ እንዲሁም ከ80 በላይ የሆኑ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተስማምተውና ተከባብረው በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድነታቸውን ጠብቀው ለዘመናት አብረው የኖሩባትና የሚኖሩባት የመቻቻል ተምሳሌትም መሆኗዋንም አስረድተዋል።
በአስተዳደሩ የጥንቲዊ የሀርላ መንደር እና ሌሎች መሰል ቅርሶቿ ለዓለም ለማስተዋወቅ እንዲሁም ጎብዎችን በመሳብ በኩል የጎላ ፋይዳ እንዳላቸውም ነው የተገለጸው።


