ከድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተሰጠ መግለጫ ።

” የዜጎችን ሰብአዊ መብት አክብሮ በማስከበር ረገድ ለአፍታም ቸል አንልም !!››

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ሙራድ መሀመድ የተባለ ወጣትን በግል ቂም በቀል በመነሳሳት ኢ-ሰብአዊ በሆነ መልኩ በመደብደብ ፤ለሞት በመዳረግ አስነዋሪ ተግባር የፈጸሙ አባላቱን በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማጣራት ላይ መሆኑን እየገለፅን ፡፡

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ‹‹በ2022 በኢትዮጵያ በላቀ ሞያዊ አገልግሎት ቀዳሚ የፖሊስ ተቋም ሆኖ ማየት››የሚል ርዕይ ሰንቆ ወደ ስራ የገባ ሲሆን ይሄንን ራዕይ ለማሳካት መላው የፖሊስ አመራር እና አባላቱ እንዲሁም ከአስተዳደሩ አመራር እና ነዋሪ ጋር በጋራ በመሆንም በተሰራው ዘርፈ ብዙ ስራዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል፡፡

እንደሚታወቀው ከለውጡ በፊት ድሬዳዋ የቀደመ ሰላሟ ርቆ ዜጎች በሰላም ወጥተው በሰላም የማይገቡበት አጅግ አስፈሪ ጊዚያት ላይ ደርሳ የነበረ ሲሆን ከለውጡ ወዲህ በተሰሩ በርካታ የፀጥታ ማስከበር ስራዎች ወደ ቀድሞ ሰላም ተመልሶ ዜጎች በነጻነት ወጥተው የሚገቡበት ባለሃብቶች መዋእለ ነዋያቸውን በነጻነት የሚያፈሱባት ከተማ መሆን ችላለቸ፡፡

በመሆኑም የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አመራር እና አባላት ይሄን አስተማማኝ ሰላም ለማምጣት እጅግ ፈታኝ የሆኑ ተግዳሮቶችን ማለፍ ፤ ቀን ከሌት በትጋት መስራት፤ ወደኋላ የሚጎትቱ መሰናክሎችን መጋፈጥ፤ ለተቀመጠ ርዕይ መሳካት አቅምን አሟጦ መጠቀም የሰርክ ተግባሩ ማድረግ በመቻሉ ነበር ፡፡

ይሁንና ሰሞኑን በጥቂት የፖሊስ አባላት ኢ-ሰብአዊ በሆነ ሁኔታ ተደብድቦ ለሞት የተዳረገ ወጣትን በተመለክተ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አመራርና አባላት በእጅጉ ያዘኑ ሲሆን የተከሰተው አስነዋሪ ተግባር የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያን በፍጹም የማይወክልና የማይገልጽ ከመሆኑም በላይ ይሄንን አስነዋሪ ተግባር በጽኑ እያወገዘ ።

‹‹በጀግንነት መጠበቅ ፤በሰብዓዊነት ማገልገል›› የሚል መሪ ቃል አንግቦ ዜጎችን ከማንኛውም ጥቃት በጀግንነት ለመጠበቅ ሌት ተቀን የሚተጋው፤ ህይወቱን በጀግንነት ለመክፈል የቆረጠው የድሬዳዋ ፖሊስ አመራርና አባላት ፤ የዜጎችን ሰብአዊ ክብር ጠብቆ ለማገለገል ቁርጠኛ አቋም ይዞ ወደ ስራ የገባው የድሬደዋ ፖሊስ ፤ የዜጎችን ሰብአዊ መብት አክብሮ በማስከበር ረገድ ለአፍታም ቸል እንደማይል እየገለፅን ።

በአሁኑ ወቅት በዚህ የወንጀል ተግባር ላይ የተሳተፉ የፖሊስ አመራርና አባላትን በፍጥነት በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ወደ ማጠናቀቅ የደረሰ መሆኑንና ነገር ግን በጉዳዩ ዙሪያ በማህበራዊ ሚድያዎች ላይ የሚሰራጩ ምስሎችና አንዳንድ መረጃዎች ከእዉነታ የራቁና መሰረተ ቢስ መሆኑን እየገለፀ በቀጣይ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ዝርዝር መረጃ ምርምራው ሂደት እንደተጠናቀቀ የምንገልፅ መሆኑን እያሳወቅን የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለተፈጸመው አስነዋሪ የወንጀል ተግባር የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በእጅጉ ማዘኑንና ፈጣሪ ለሟች ቤተስቦችና ወዳጆች ሁሉ መጽናናትን ይመኛል ።

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ

ታህሳስ 27.2017 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *