በድሬዳዋ አስተዳደር በድምቀት እየተከበረ የሚገኘውን የጥምቀት ቃና ዘገሊላ በአል በማስመልከት የርእሳነ አድባራትወ ገዳማት ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ታቦት ከባህረ ጥምቀቱ ወደ መንበሩ የሚሸኙ ምእመናንን ጣፋጭ ምግቦች ፣ ፍራፍሬዎችና ቀዝቃዛ ውሃዎችን በማዘጋጀት አብሮነታቸውንና ፍቅራቸውን እየገለጹ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታይ እህትና ወንድሞች እያደረጉት ያለው መስተንግዶ የድሬዳዋ መልክና ውበት ማሳያ ነው፡፡

የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የትምህርት ክፍላ ኃላፊና የድሬዳዋ አስተዳር የሓይማኖትቋማት ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ ሊ ብርሃናት ቀለመወርቅ አለሙ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታይ እህትና ወንድሞች እያደረጉት ያለው መስተንግዶ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ሊወረስ የሚገባው የፍቅር ተግባር ነው ያሉ ሲሆን ይህንን ያስተባበሩ እህት ወንድሞች በሙሉ ፈጣሪ ይባርካቸው ሲሉም የቡራኬያቸውን ሰጥተዋል፡፡

የወረዳ 6 ነዋሪዋ ቴይሲር ሰኢድ ይህ ዛሬ የእስልምና እምነት ተከታይ እህትና ወንድሞች የምናደርረገው መስተንግዶ ከባእላት ውጪም በአዘቦት ቀና አብረን የምንኖረው የማህበራዊ ህይወታችን ማሳያ መልካችን ነው ፣ እኛም በአላችንን ስናከብር የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ወንድሞችና እህቶች እንደዚሁ በሚያምርና ውበትና ፍቅራችንን በሚያጎላ ሁኔታ ያስተናግናል ብላለች፡፡

የወረዳ 6 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አባስ አሊ በበኩላቸው ይህ በበአላት ወቅት የድሬዳዋ ውበት አምሮና ጎምርቶ የሚታይበ ጊዜያችን ነው ፡፡ ድሬዎች የእስልምናና የክርስትና ሃይማኖት በአላት ፍቅራችንን የምናጎላበት ልዩ የመድመቂያና የማቢያ ጊዜያችን ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ለድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒጀኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገልጸዋል፡፡

የወረዳ 03 የእስልምና እምነት ተከታይ እህትና ወንድሞችም በተመሳሳይ በአካባቢያቸው ታቡቱን አጅበው ወደ ማደሪያ መንበሩ ለሚሸኙ ምእመናን ጣፋ3 ምግቦች ፣ ፍራፍሬዎችና ውሃ በማዘጋጀት ሲያስተናግዱ ያገኘናቸው ወይዘሮ አዚዛ ሱሌይማን በበኩላቸው ይህ አይነቱ ውበታችን በበአላት ወቅት ጎልቶና ደምቆ የሚወጣ የድሬዳዋዎች መገለጫ መልክ ነው ብለዋል፡፡

ከወረዳ 03 በተመሳሳይ ሁኔታ ለምእመናን መስተንግዶ ሲያደርጉ ካገኘናቸው የእስልምና እምነት ተከታይ እህቶች መካከል ሊና ሬድዋንም እንደዚህ ያለው አንዳችን ለሌችን የሃይማኖት ልዩነት ሳይገድበን የምናደርገው ትብብር ፍቅር የወለደው የድሬዳዋ መልክና መገለጫ ውበታችን የእኛነታችን ገጽታ ነው ብላለች፡፡

ዳንኤል አማረ

ምስል ቴዎድሮስ ልኡል ሰገድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *