የድሬዳዋ አስተዳደር የ 2017 በጀት ዓመት የ 2 ተኛ ሩብ አመት የማዘጋጃ ቤታዊ ፣ የሴክተር ተቋማት ፣ የከተማና ገጠር ወረዳዎች የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል

የስራ አፈፃፀም ሪፖርቱን የአስተዳደሩ የፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኃይለማርያም ዳዲ ያቀረቡ ሲሆን በግብርና ሆርቲካልቸር ልማት ባለፍት 6 ወራት 6,825 አርሶ አርብቶ አደሮችን የኤክስቴንሽን አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ 6,631 አርሶ አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለና ከነዚህም ውስጥ 67.3 % አባወራ 32.7 % እማወራም መሆናቸውን ነው በሪፖርቱ ላይ የተገለፀው ።

የህብረት ስራ ማህበራትን ሪፎርም ከማድረግ አኳያ በስድስት ወሩ በገጠር 2 እንዲሁም በከተማ 6 ማህበራትን ሪፎርም ለማድረግ ታቅዶ እቅዱ ሙሉ በሙሉ ተከናውኗል ። 16,025,000 ተጨማሪ ካፒታል ለማፍራት ታቅዶ ወደ 47,569,592 ማፍራት እንደተቻለና ከቁጠባ አንፃር 19,250,000 ለማሰባሰብ ታቅዶ 43,974,543 ለማሰባሰብም ተችሏል ።

በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ክላስተር ልማት የመሰረተ ልማት አቅርቦትና ዘላቂነትን 10 ሳይት የሚከሰቱ የኤሌክትሪክ መስመር እና የውሀ ብልሽቶችን የጥገና ስራ እና አዲስ 10 ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ጥያቄዎች 9 የውሀ መስመር ጥያቄዎችን በአግባቡ ማስተናገድና ምላሽ የመስጠት ስራም ተሰርቷል ። የአምራች ኢንዱስትሪዎች የመስሪያ ቦታዎች ላይ 3 ዙር ክትትል በማድረግ በ 54 ህገ-ወጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ማስተካከያ እርምጃዎችን የመውሰድ ተግባራት ተከናውኗል ።

የስራ ክህሎት እና ቴክኖሎጂ ልማትን በተመለከተ የክህሎት ስልጠና ፍትሀዊነት ተደራሽነትን ከማሳደግ አንፃር በግማሽ አመቱ በተቋማት 2,689 ገበያ ተኮር አጫጭር ስልጠና ሰልጣኞችን ለመቀበል ታቅዶ 2,657 ሰልጣኞች ቅበላም ማድረግ ተችሏል ።

ከዚህ በተጨማሪም የክህሎት ስልጠና እና ጥራትን ከማሻሻል አንፃር በግማሽ አመቱ 40 የሙያ ደረጃዎችን ለኢንዱስትሪ እና ለተቋማት ለማሰራጨት ታቅዶ በእቅዱ መሰረት 40 የሙያ ደረጃዎችን የማሰራጨት ስራም የተከናወነ ሲሆን የክህሎት ልማት ፣ ብቃት ፣ ፍትሀዊነት ፣ ተደራሽነት ፣ አግባብነት እና ጥራት ከማሳደግ አንፃር በግማሽ አመቱ ለ 95 አሰልጠኞች ፣ አመራሮች እና ባለሞያዎች እንዲሰለጥኑ እና ልምድ እንዲያገኙ ታቅዶ ለ 78 ቱ ስልጠና በመስጠት የእቅዱን ( 82.1 ) ማከናወንም ተችሏል ።

በአለማየሁ አበበ

ፎቶ :- አገኘው ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *