የገባነውን ቃል ወደ ባህል ለመለወጥ እንሠራለን!”ከንቲባ ከድር ጁሃር

የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት ከቃል እስከ ባህል በሚል መሪ ቃል ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ባሳለፍነው ሳምንት ማካሄዱ ይታወሳል ፡፡

በጉባኤውም በአንደኛ መደበኛ ጉባኤ የተገቡትን ቃሎች ወደ ባህል ለመለወጥ የተሰሩና በቀጣይ በሚሰሩ ተግባራት ዙሪያ የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሃር መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም የነበረበትን የሠላምና የፀጥታ መደፍረስ ችግር ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ መቅረፍ መቻሉንና ድሬዳዋ ከዚህ ቀደም ትታወቅበት ወደ ነበረበት የወንድማማችነት ፍቅርና እንግዳ በሰላም የሚያርፍባት ከተማ ለማድረግ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል፡፡

ከንቲባው አያይዘውም ድሬዳዋን ፍትህ የሰፈነባት ሁሉም ማህበረሰብ ተቻችሎና ተከባብሮ የሚኖርባት ከተማ ለማድረግ የፀጥታ ችግሮችን ሰው ተኮር በሆነ መልኩ እንዲፈቱ መደረጉን ተናግረው፤ በዚህም የፖሊስ ሃይልና የገጠር ሚሊሻን በማጠናከር፣ የትራንስፖርትና የትራፊክ እንቅስቃሴን በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል፡፡

በቀጣይ በኮሪደር ልማት ስራው ደግሞ በየመንገዱ ካሜራዎችን በመግጠም የፊት እየታ ልየታ በማድረግ ወንጀለኞችን በቀላሉ ለመያዝ በመጠቀም ጥፋተኞችን ለህግ በማቅረብ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥና ፍትህን ለማስፈን እንደሚሰራም ነው ክቡር ከንቲባው በመግለጫቸው ያስታወቁት ፡፡

በኢኮኖሚ ዘርፍ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ያስቻለ ነፃ የንግድ ቀጠና ያላት፤ በቀን ከ1050 በላይ ከባድ መኪኖች የሚተላለፉባትና ለደረቅ ወደብም ምቹ በመሆኗ ሰላሟን በዲጅታል በታገዘ መልኩ መጠበቅ የእለት ተዕለት ተግባር ተደርጎ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ድሬዳዋን ሰላምና ፀጥታዋ የተከበረ ለማህበረሰቡም ምቹ የሆነች ከተማ ለማድረግ የተጣለብንን ሃላፊነት ለመወጣት ተግተን እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ከንቲባው በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡

በሄለን ሽጉጤ

ፍቶ፦አገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *