አንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ በሚል መርሃግብር የክረምት የሙያ ክህሎት ስልጠናን ሲከታተሉ የነበሩ ከ250 በላይ ወጣቶች ተመረቁ::

በድሬደዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ዜጎች ቢያንሰ የአንድ ክህሎት ባለቤት እንዲሆኑ ለማድረግ “አንድ ሞያ ለአንድ ዜጋ” በሚል መሪ ቃል የወጣቶች የክረምት ስልጠናን ሲከታተሉ የነበሩ 270 ወጣቶችን አስመርቋል።

በኹነቱ ላይ የተገኙት የቢሮው ሀላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ያለፉትን 3 ወራት በ14 ዘርፎች የተሰጠውን ክህሎት መር ሰልጠና የእረፍት ጊዜያቸውን በመሰዋት ወስደው የተመረቁት ወጣቶቹ ህብረተሰቡ ለዘርፉ ያለውን የተዛባ አመለካከት በመቀየር በኩል የተጣለባቸውን ሀላፊነት ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

የአንድን ሀገር እድገትን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ቢያነስ የአንድ ሞያ ባለቤት የሆነ የሰለጠነ ዜጋ ማፍራት አስፈለጊ መሆኑን የገለፁት ሀላፊው በክረምት አጫጭር ሞያዎች ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች ስራን በራሳቸው በመፍጠር በኩል አይነተኛ ክህሎት መቅሰማቸውን ገልፀዋል።

የቢሮው ምክትል ሀላፊ እና የቴክኒክ እና ሞያ ትምህርትና ስልጠና ማስፋፊያ ኤጀንሲ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በበኩላቸው ተቋሙ ባለፉት ሁለት አመታት በዘርፉ በረካታ ወጣቶችን የሞያ እና የክህሎት ባለቤት ማድረጉን ጠቅሰው ስልጠናው ወጣቶች ያላቸውን ዝንባሌ በጊዜ አውቀው ክህሎታቸውን እንዲያሳደጉ ያገዘ እንደሆነ አሰታውቀዋል።

ሰልጣኞች በበኩላቸው የወሰዱት የክህሎት ስልጠና የወደፊት ህይወታቸውን የተቃና በማድረግ በተለይም የራሳቸውን ሞያ ተጠቅመው ሥራ እንዲፈጥሩ አይነተኛ ድጋፍ እንደሚደርግላቸው ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *