ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመስከረም እና ጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም በመሠረተ ልማት፣ በገጠር ልማት፣ በአስተዳደራዊ ማሻሻያ እና በዲፕሎማሲያዊ ትብብር ላይ ያተኮሩ ተከታታይ አገራዊ እና ዓለም አቀፍ ተግባራትን አከናውነዋል። ያለፈውን ወር ተግበራት በጨረፍታ እነሆ፥

የከተማ ልማት እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመተባበር ለሚገነባው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ እና በጎልደን ኮንኮርድ ግሩፕ አማካኝነት ለሚገነባው የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ መሠረት መጣላቸው ከካናወኗቸው ቀዳሚ ተግባራት የሚጠቀሱ ናቸው። የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ከሂላል የነዳጅ ስፍራ ድፍድፍ ነዳጅ በማውጣት፣ በማጣራትና በማጠራቀም በዓመት 3.5 ሚሊዮን ቶን…

Read More

ባለፉት 3 ወራት ብቻ በተመረቱ ተኪ ምርቶች ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል – የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው ሲል የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ። መንግሥት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለማምረት እንዲቻል የተኪ ምርት ስትራቴጂን በመቅረጽ ወደ ሥራ በመግባቱ ከፍተኛ ውጤቶች ተመዝገበዋል ብሏል አገልግሎቱ በመግለጫው። ስትራቴጂው የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲኖር፣ የወጪ-ገቢ ምርት እንዲመጣጠን እና ሀገራዊ ሉዓላዊነት እንዲረጋገጥ እያደረገ ይገኛልም ነው ያለው።…

Read More