ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህንድ አቻቸዉ ናሬንድራ ሞዲ እና ከልዑካን ቡድናቸዉ ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ለህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ይፋዊ አቀባበል ሥነሥርዓት አድርገናል ብለዋል፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት ካደረግን በኋላ ከልዑካን ቡድኖቻችን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል። በውይይታችን በኢትዮጵያ እና ህንድ መካከል እያደገ የመጣውን ትብብር እና የወል ቅድሚያዎች የሚያንፀባርቁ አዳዲስ የትብብር መስኮችን ቃኘተናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በሁለቱ ሀገራት መካከል…


