ባለፉት 3 ወራት ብቻ በተመረቱ ተኪ ምርቶች ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል – የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው ሲል የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ። መንግሥት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለማምረት እንዲቻል የተኪ ምርት ስትራቴጂን በመቅረጽ ወደ ሥራ በመግባቱ ከፍተኛ ውጤቶች ተመዝገበዋል ብሏል አገልግሎቱ በመግለጫው። ስትራቴጂው የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲኖር፣ የወጪ-ገቢ ምርት እንዲመጣጠን እና ሀገራዊ ሉዓላዊነት እንዲረጋገጥ እያደረገ ይገኛልም ነው ያለው።…


