የብልፅግና ፓርቲ የ2018 ዓመታዊ የከፍተኛ አመራሮች ሥልጠናውን እያካሄደ ነው።
ሥልጠናው “በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሐሳብ ለሚቀጥሉት 10 ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ሥልጠናው የአመራሩን እውቀት፣ ክህሎት እና አቅም የሚገነቡ ልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮች የሚቀርቡበት መሆኑን ፓርቲው አስታውቋል።
በሥልጠናው ከ2000 በላይ ከፌዴራል እና ከክልል የተወጣጡ ከፍተኛ አመራሮች እንደሚሳተፉ ነው የተገለጸው።
ከሥልጠናው በተጓዳኝ የተግባር የመስክ የልማት ስራ ጉብኝቶች የሚካሄድ መሆኑን ከፓርቲው የማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።


