በአስተዳደሩ ከህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በሰሌዳው የመጨረሻ ቁጥር በፈረቃ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል::
ይሁንና ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ ያለውን የስምሪት ስርአት ላይ ማስተካክያ በማድረግ አሁን ካለው ሂደት ጋር አጣጥሞ ለመምራት ሲባል ከዚህ በታች የተመለከቱት ማስተካከያዎች ከጥቅምት 16 ቀን 2013 አ.ም ጀምሮ ተደርገዋል::
1ኛ፦ተማሪዎችን ትምህርት ቤት የሚያደርሱ የትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ከተፈቀደላቸው ቀን ውጪ አገልግሎት ለመስጠት ከተማሪዎቹ ትምህርት ቤት ይህንኑ የሚያስረዳ ደብዳቤ በማፃፍ ከመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ቀርበው ፍቃድ መውሰድ የምትችሉ ሲሆን ይህንኑ ፍቃድ ይዞ መንቀሳቀስም ይጠበቅባችሃል ::
2፦ከፈረቃ ቀን ውጪ ለተማሪዎች ትምህርት ቤት መውሰጃና መመለሻ በተሰጠው ፍቃድ መንቀሳቀስ የሚቻለው በተማሪዎች መግቢያና መውጫ ሰአት ለተማሪዎቹ አገልግሎት ለመስጠት ብቻ ይሆናል ::
በመሆኑም ለተማሪዎች አገልግሎት እንዲሰጥ ከላይ ከተፈቀደው አግባብ ውጪ በሆነ መልኩ ህግና አሰራርን ጥሶ በሚያሽከረክር አሽከርካሪ ላይ ተገቢው ቁጥጥርና የትርምት እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል::
የፌ/መ/ት/ባ/ድ/ዳ/ፅ/ቤትና የትራፊክ ፖሊስ ዳሪክቶሬት
ጥቅምት 14 ቀን 2013 አ.ም


