የፓርቲው የ1ኛ ሩብ የስራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል::

    በመድረኩ የፓርቲው ጽ/ቤት የ2012 በጀት የስራ አፈጻጸም ሪፓርት፣ የ2013 ጥቅል እቅድ እና የዘርፎች የ2013 1ኛ ሩብ አፈጻጸም ተገምግሟል።
    በፓርቲው ስር የታቀፉ 5 ዘርፎች ማለትም የአደረጃጀት ዘርፍ፣ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ፣ የጥናት ምርምርና ሱፐርቪዥን ዘርፍ፣ የህዝብ ግንኙነትና ሲቪክ ማህበራት ዘርፍ እና የልማታዊ ተቋማት እቅድ ክትትልና ድጋፍ ዘርፍ የ1ኛ ሩብ ስራ አፈጻጸም ረፖርት ዘርዘር ባለ ሁኔታ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።
    እያንዳንዱ ዘርፍ ያቀረቡትን ሪፖርት መነሻ በማድረግ የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን በቀረቡት ላይ የዘርፍ ኃላፊዎችና በስሩ የታቀፉ የመምሪያ ኃላፊዎች መልስ ሰጥተውበታል።
    በመድረኩ ማጠቃለያ የፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ በሪፖርቱና ቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ የስራ አቅጣጫ በማመላከት የግምገማ መድረኩ ተጠናቀቀ።